Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ovsjg

Office of Victim Services and Justice Grants
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

Private Security Camera Incentive Program FAQs - Amharic (አማርኛ)

የግል ደህንነት ካሜራ ማበረታቻ ፕሮግራም
 
ኤፍኤኪው 
 
1. ልዩ አይነት የደህንነት ካሜራ ሲስተም መግዛት አለብኝ?
ልዩ አይነት የደህንነት ካሜራ ሲስተም ለመግዛት ግዴታ ባይኖርም፣ አንዳንድ ዝቅተኛ እና የሚመከሩ ዝርዝር መግለጫዎች አሉ።
 
2. የደህንነት ካሜራው(ዎች)ን በተወሰነ ቦታ ላይ መገጠም ይኖርበታልን? 
ካሜራዎች በህንጻው ውጫዊ አካል ላይ መገጠም አለባቸው።  
 
3. ምላሹ ስንት ነው?
አመልካቾች ለደህንነት ካሜራ ምላሽ በካሜራ እስከ $200 ለመኖሪያ አድራሻ የመጨረሻው ትልቁ ምላሽ እስከ $500 እንዲሁም ለሌሎች አድራሻዎች $750 ማመልከት ይችላሉ።
 
4. ከአንድ በላይ ለሆኑ ካሜራዎች ምላሽ ማግኘት ይቻላል? 
አዎ። ምንም እንኳ በቦታ አድራሻ አንድ የደህንነት ካሜራ ሲስተም ብቻ የሚፈቀድ ቢሆንም አንድ (1) የካሜራ ሲስተም ብዙ ካሜራዎችን ማካተት ይችላል። ከአንድ በላይ ለሆኑ ካሜራዎች ለምላሹ ማመልከት ይችላሉ፤ ይህም ምላሹ በካሜራ እስከ $200 ፣ ለመኖሪያ አድራሻ የመጨረሻው ትልቁ ምላሽ እስከ $500 እንዲሁም ለሌሎች አድራሻዎች $750 እስካላለፈ ድረስ ነው።
 
ለምሳሌ፥:
አንድ ነዋሪ ሁለት (2) ካሜራዎች ያሉት የካሜራ ሲስተም ለያንዳንዱ ካሜራ $200 ከገዛ፣ የምላሽ መጠይቁ $400 መሆን አለበት።
አንድ ነዋሪ ሶስት (3) ካሜራዎች ያሉት የካሜራ ሲስተም ለያንዳንዱ ካሜራ $300 ከገዛ፣ የምላሽ መጠይቁ $500 መሆን ሲኖርበት፣ ምክንያቱም የሚፈቀደው በካሜራ $200 ሲሆን፣ በቤት አድራሻ ትልቁ ምላሽ $500 ነው። 
አንድ ንግድ ቤት ስድስት (6) ካሜራዎች ያሉት የካሜራ ሲስተም ለያንዳንዱ ካሜራ $150 ከገዛ፣ የምላሽ መጠይቁ  $750 መሆን ሲኖርበት፣ ምክንያቱም ለንግድ ቤት የሚፈቀደው ትልቁ ምላሽ $750 ነው።  
 
5. ምላሹን ለመቀበል ምን ያህል ጊዜ ይፈጃል?
ማመልከቻውን እንደላኩ፣ ማመልከቻው ከተሟላ እና ከተፈቀደ፣ ምላሹን ለማግኘት እስከ 45 የስራ ቀናት ድረስ ይፈጃል። 
 
6. ኮምፒዩተር ከሌለኝ ለግል ደህንነት ካሜራ ማበረታቻ ፕሮግራም ማመልከቻውን እንዴት አድርጌ መላክ እችላለሁ?
በከተማው የተለያዩ ቦታዎች ኮምፒዩተር አገልግሎት የሚያቀርቡ አሉ። ለነጻ የኮምፒዩተር አገልግሎት ሰጪዎች ዝርዝር በ http://connect.dc.gov/service/public-computer-access. ይገኛል። እንዲሁም “FIND” የሚለውን ቃል በቴክስት ለ 83224 ወይም በ (202) CONNECT (202-266-6328) ይደውሉ።
 
7.  ከዲሲ ሜትሮፖሊታን ፖሊስ ክፍል (ኤምፒዲ) ጋር ካሜራዬን እንዴት ነው የማስመዘግበው
 
8.   https://octo.quickbase.com/db/biickd9gf?a=nwr በመጎብኘት ቅጹን ይሙሉ። ለምላሹ ለማመልከት ምን
      አይነት ዶክመንቶች ያስፈልጉኛል? 
የደህንነት ካሜራ ሲስተሙ የተገዛበት ማረጋገጫ
ከኤምፒዲ ጋር የተመዘገበበት ማረጋገጫ
አመልካቹ ተከራይ ከሆነ፣ የንብረቱ ባለቤት ፈቃድ የሰጠበት ዶክመንት
የደህንነት ካሜራ ሲስተሙ የተገጠመው ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ባለው የደህንነት ሲስተሞች መግጠም ላይ በተሰማራ የንግድ ኩባንያ ከሆነ፣  በቦታው ላይ መገጠሙን ማስረጃ 
 
If ተጨማሪ ማስረጃ ካለዎት፣ እባክዎትን ፕሮግራሙን በ [email protected] ወይም በ 202-727-5124 ያግኙ።