Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ovsjg

Office of Victim Services and Justice Grants
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

የአድራሻ ሚስጥራዊነት ፕሮግራም

የዲስትሪክቱ የአድራሻ ሚስጥራዊነት ፕሮግራም (ACP)፣ በተጠቂ አገልግሎቶች እና ፍትህ አሰጣት ቢሮ (OVSJG) የሚተዳደር፣ ብቁ ለሆኑ የዲሲ ኗሪዎች የትክክለኛ አድራሻቸውን ሚስጥራዊነት ለመጠበቅ ህጋዊ ተተኪ አድራሻን ይሰጣል። ለደህንነታቸው ስጋት ያለባቸው ኗሪዎችን ያግዛል፣ የጎዳና አድራሻቸውን ከህዝብ መዝገቦች በመደበቅ፣ እና በሰፊው የግለሰብ የደህንነት እቅድ ውስጥ አንድ መሳሪያን በማቅረብ።

ACP እንዴት ይሰራል?

ተተኪ አድራሻ 
ብቁ የሆኑ አመልካቾች የACP መፍቀጃ ካርድን ከተተኪ አድራሻ ጋር ይቀበላሉ። ይህ ካርድ የእውነተኛ ቤታቸው፣ ስራቸው፣ ወይም የትምህርት ቤት አድራሻቸው ቦታ ለማንኛውም የዲስትሪክት ኤጀንሲ በተሳታፊዎች ይቀርባል። የዲስትሪክት ኤጀንሲዎች ተተኪ አድራሻን እንዲቀበሉ በህግ ይጠየቃሉ።  

ፖስታን አሳልፎ መላክ 
ACP የሁሉም ተሳታፊ የመጀመሪያ-ደረጃ፣ የተረጋገጠ፣ ወይም የተመዘገበ ፖስታን ይቀበላል እና ፖስታውን ወደ ተሳታፊ አካላዊ አድራሻዎ ይልካል። 

ገደቦች 
ተተኪ አድራሻ የተሳታፊ ትክክለኛ አድራሻ በሌሎች መንግስታዊ-ያልሆኑ ኤጀንሲዎች እንደማይጠየቅ ዋስትና አይሆንም። ይህ ፕሮግራም ህዝባዊ የግል መረጃን እንደገና ማደስ ውስጥ አያግዝም። በተጨማሪ፣ ACP ትርኪ ምርኪ ፖስታዎችን፣ እሽግ መልዕክቶችን፣ ወይም ጋዜጣዎችን አሳልፎ አይልክም፤ የመብት ተከራካሪ ወይም የማመልከቻ ረዳት ያንን ፖስታ በደህንነት ለመቀበል እንዲያቅዱ አመልካቾችን ሊረዱዎት ይችላሉ። ሌሎች ገደቦች በተጨማሪ መተግበር ይችላሉ።

ለማን ነው የሚሰጠው?
ግለሰቦች በሚከተሉት ሁኔታዎች ውስጥ ለACP ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ፥ 
(1) ለደህንነታቸው ስጋት ከገባቸው፤ 
(2) ባሁን ጊዜ (ወይም በቅርብ ጊዜ ውስጥ) የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ፤ እና 
(3) የቤት ውስጥ ጥቃት፣ ጾታዊ ጥቃት፣ መከታተል፣ ወይም የሰው ዝውውር ጥቃት አጋጥሞት ከሆነ፤ ወይም ዋና ዓላማቸው ከላይ የተጠቀሱ ጥቃቶች የደረሱባቸው ተጠቂዎችን ማገልገል የሆነ ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው ከሆነ፤ ወይም የስነ-ተዋልዶ ጤና እንክብካቤ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው ከሆነ። 
በተጨማሪም አመልካቾች የሚከተሉትን እንዲያደርጉ ይፈለጋሉ፥ ባለፉት 60 ቀናት ውስጥ የተዘዋወሩ መሆን፣ በሚቀጥሉት 30 ቀናት ውስጥ ለመዛወር እያቀዱ መሆን፣ ወይም ያሁኑ አድራሻቸው በኦንላይን ወይም በህዝብ መዝገቦች አማካኝነት በቀላሉ እንዳይገኙ ለመረጋገጥ በቂ እርምጃዎችን የወሰዱ መሆን። ሁለቱም አዋቂዎች እና ልጆች ሊያመለክቱ ይችላሉ።

ማመልከቻው እንዴት ይፈጸማል

የማመልከቻ  አጋዦችጥያቄዎችን ለመመለስ፣ ብቁነትን ለማረጋገጥ፣ እና ማመልከቻዎችን ለመቀበል በዲስትሪክቱ ውስጥ ያሉ በርካታ ኤጀንሲዎች ውስጥ ይገኛሉ። እንዲሁም እነሱ የመብት ክርክር አገልግሎቶችን ማቅረብ እና በግል ፍላጎቶች መሰረት ሁለንተናዊ የደህንነት እቅድ ለማዘጋጀት ሊረዱ ይችላሉ። 

ስለ ACP የበለጠ ለማወቅ ወይም ማመልከቻዎችን ለማስገባት የሚከተለው ዝርዝር ላይ በተዘረዘሩ ማንኛውም ድርጅቶች ውስጥ ያሉ የማመልከቻ ረዳቶችን ያግኙ።

የማመልከቻ ረዳቶች ዝርዝር
 
የተደራሽነት መገልገያዎች፥
የACP ፕሮግራም በራሪ ወረቀት