Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ovsjg

Office of Victim Services and Justice Grants
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

የግል ደህንነት ካሜራ ማበረታቻ ፕሮግራም

የፕሮግራም መግለጫ  

የግል ደህንነት ካሜራ ማበረታቻ ፕሮግራም የሚ ተዳደረው በተጠቂዎች አገልግሎት እና ፍትሕ ልገሳ (ቢሮ) ሲሆን ለነዋሪዎች፣ ንግድ ቤቶች፣ ለትርፍ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ እና የሃይማኖት ተቋማት የደህንነት ካሜራ ሲስተሞችን በቦታቸው ላይ እንዲተክሉ እና ከሜትሮፖሊታን ፖሊስ ዲፓርትመንት (ኤምፒዲ) ጋር እንዲመዘገቡ ምላሽ ይፈጥራል። ፕሮግራሙ የሚያቀርበው ምላሽ በካሜራ እስከ $200 ፣ ለመኖሪያ አድራሻ የመጨረሻው ትልቁ ምላሽ እስከ $500 እንዲሁም ለሌሎች አድራሻዎች $750 ነው። ይህ ፕሮግራም ወንጀልን ለመከላከል እና ህግ አስከባሪዎችን በምርመራ ለመርዳት ያግዛል። 
መስፈርቶች  
የካሜራ ሲስተሙ ከ ሴፕቴምበር 22, 2015 በሁዋላ የተገዛ እና የተገጠመ እንዲሁም ሁሉም ያሉት ፈንዶች ከማለቃቸው በፊት መሆን አለበት። እንዲሁም ካሜራው ከሜትሮፖሊታን ፖሊስ ዲፓርትመንት ጋር መመዝገብ አለበት። የምላሹ መጠን የካሜራ ሲስተሙ ከተገዛበት ዋጋ መብለጥ የለበትም። በያንዳንዱ ቦታው አድራሻ ላይ የሚፈቀደው ለአንድ የደህንነት ካሜራ ብቻ ነው። የደህንነት ካሜራ ሲስተሞቹ በህንጻው ውጭ ላይ መገጠም አለበት። አመልካቾች የሲስተሙን መገጠም ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል (ለተሟላ ዝርዝሮች ማመልከቻውን ይመልከቱ) 
 
የካሜራ ሲስተም ዝርዝሮች
ዲጂታል ካሜራዎች ዝቅተኛ መለኪያዎች የሚመከሩት መለኪያዎች
ካሜራ ሬዞሉሽን
1 ሜጋፒክሴል 3 ሜጋፒክሴል
ስክሪን ሬዞሉሽን 1280x1024 2048x1536
የቪዲዮ ጥራት መደበኛ ከፍተኛ 
ፍሬሞች በሰከንድ 5 15
የሚጠየቀው ዲቪዲ ክምችት  200 ጂቢ በካሜራ 2.5 ቲቢ በካሜራ
 
ዝቅተኛ መለኪ        ያዎች የሚመከሩት መለኪያዎች 
ስክሪን ሬዞሉሽን 640X480 640X480
ፍሬሞች በሰከንድ 5 15
የሚጠየቀው ዲቪዲ ክምችት 125 ጂቢ በካሜራ 350 ጂቢ በካሜራ 

ገደቦች  
አመልካቾች በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ የሚገኝ መኖሪያ ቤት፣ ንግድ ቤት፣ ወይም ለትርፍ ያልሆነ ወይም የሃይማኖት ድርጅት ባለቤት ወይም ተከራይ መሆን አለባቸው። ተከራይ የሆኑ አመልካቾች ከንብረቱ ባለቤት የደህንነት ካሜራ ሲስተም በቦታው እንዲገጠም የፈቀዱበትን ዶክመንት ማቅረብ አለባቸው። እስከ ጁላይ 31, 2016, ድረስ፣ ቢሮው ማመልከቻ የሚቀበለው የአመልካች ቤቶች በተወሰኑ የፖሊስ አገልግሎት ቦታዎች ላይ የሚገኙትን ነው። ከኦገስት 1, 2016, ጀምሮ፣ የሚቀር ፈንድ እስካለ ድረስ፣ በቀጠና ውስጥ የሚገኙ ቦታዎች በፕሮግራሙ ላይ መሳተፍ ይችላሉ።  
 
 
የፕሮግራሙን ዝርዝር መጠይቅ ለማየት፣ የደህንነት ካሜራ ማበረታቻ ፕሮግራም ማመልከቻ መጠይቅ ዶክመንትን ይጠቀሙ።
 
ማመልከቻ  
 
ተያያዥ(ዦች) 
ለደህንነት ካሜራ ማበረታቻ ፕሮግራም መጠይቅ ማመልከቻ   
ማመልከቻ